|
ስርዓቶቻችን ይበልጥ ተገቢ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ለእርስዎ ለማቅረብ እንደ የGmail ኢሜይሎች ያሉ በአገልግሎታችን ውስጥ ያሉ ይዘቶችን በራስ-ሰር ሊቃኙ ይችላሉ። ስለዚህ ለምሳሌ በቅርቡ ስለፎቶግራፊ ወይም ካሜራዎች ብዙ መልዕክቶች ከደረሰዎት በአንድ አካባቢያዊ የካሜራ መደብር ውስጥ ስላለ ቅናሽ ማወቅ ሊፈልጉ ይችሉ ይሆናል። በሌላው በኩል ደግሞ እነዚህን መልዕክቶች አይፈለጌ መልዕክት ብለው ሪፖርት ካደረጓቸው ያንን ቅናሽ ማየት የማይፈልጉ ሳይሆኑ አይቀሩም። ይህ አይነት የራስ-ሰር ሂደት ብዙ የኢሜይል አገልግሎቶች እንደ የአይፈለጌ መልዕክት ማጣሪያ እና ፊደል ማረሚያ ያሉ ባህሪያትን የሚያቀርቡበት መንገድ ነው። በGmail ውስጥ ያለ የማስታወቂያ ማነጣጠር ሙሉ ለሙሉ በራስ-ሰር የሚሰራ ነው፣ እና ማስታወቂያዎችን ወይም ተዛመጅ መረጃን ለእርስዎ ለማሳየት ማንም የሰው ፍጡር ኢሜይልዎን ወይም የGoogle መለያ መረጃዎን ማንበብ አይችልም። በGmail ውስጥ ስላሉ ማስታወቂያዎች እዚህ ተጨማሪ ይወቁ።
|