|
የቬጂታኒ ሆስፒታል የአጥንት ህክምና ክፍል አጠቃላይ የምርመራ፤የህክምና እና የአጥንት ቀዶ ጥገናን ያሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ማዕከል ነው፡፡አገልግሎቶቻችን በአደጋም ሆነ በተፈጥሮ ምክኒያት የሚመጡ ስብራት እና የውልቃት ችግሮችን ማስተካከል፤የስፖርት ህክምና ማማከር አገልግሎት፤የመገጣጠሚያ መቆጣት ህክምና፤ያልተመጣጠኑ እግሮችን ማስተካከል፤እጅ ላይ የሚፈጠሩ ግድፈቶችን ማስተካከል፤የጀርባ ህመም ህክምና፤የዲስክ መንሸራተት እና ሌሎች ከአጥንት እና ጡንቻ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ችግሮች ያጠቃልላል፡፡የታካሚዎችንም ችግር ለማወቅ ወይም ለመመርመር እና ለማከም የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎችን ያሟላ ነው፡፡ሀኪሞቻችንን እንዲሁም አብረዋቸው የሚሰሩት ነርሶች የላቀ እውቀት ያላቸው እና የሀገሩንም ሰው ሆነ ከመላው አለም የሚመጡ አለም አቀፍ ታካሚዎችን በማገልገል ልምድ ያላቸው እንዲሁም ተወዳዳሪ የሆኑ ናቸው፡፡ ቬጂታኒ ሆስፒታል ከአለም አቀፍ ጥምር ኮሚሽን(JCI) እውቅናን ያገኘ ሲሆን ይህም ማለት በሆስፒታሉ የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆናቸውን ያረጋግጣል፡፡
|